ይፋት ልማት ማህበር
የማህበሩ ዋና ዓላማ:- ማህበሩ ከአባላቱ፣ ከአካባቢው ማህበረሰብ፣ ከሌሎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ግለስቦች እና ለጋሽ አካላት የሚያገኘውን የገንዘብ፣የአይነት እንዲሁም የዕውቀት ድጋፍ በማስተባበር በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር በይፋት አካባቢ ማለትም በጣርማበር፣ በቀወት ፣በኤፍራታናግድምና በአንጾኪያና ገምዛ ወረዳዎች እንዲሁም በደብረሲና ፣በሸዋሮቢትና በአጣዬ ከተማ አሰተዳደሮች፣ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንቅስቃሴዎች ውስጥ በመሳተፍ ዘላቂ ልማትን (Sustainable development) ለማረጋገጥ የሚደረገዉን ጥረት መደገፍ ነው። እንዲሁም አዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች በማህበራዊ ዘርፍ ድጋፍ ማድረግ፡፡
ተልዕኮ
በተመረጡ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ ፣ መሰረተ ልማት እና የመልካም አስተዳደር ዘርፍ መርሃ ግብሮች እና ፕሮጀክቶች በጋለ ስሜት እና በትጋት ስርዓት በምሳሌነት ደረጃ የ ”ይፋት” ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሁለገብ እና ዘላቂ ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ልማት ምሳሌያዊ ልማት ድጋፍ ማድረግ
ራዕይ
በተሟላ ሁኔታ ፣ በዘላቂነት የተሻሻለ እና የተለወጠ ይፋት በ2023 !
ስትራቴጂ
የአከባቢውን ማህበረሰብና ሀብት መሰረት ያደረገ ኢንዱስትሪያላይዜሽን እና ዘመናዊነት መፍጠር !!