በይፋት ላመት ማህበር የክረምት በጎ አድራጎት
የማጠናከሪያ ትምህረት
2013 ዕቅድ
I. መግቢያ
ይፋት ልማት ማህበር ከተቋቋመ አጭር ጊዜዉ ቢሆንም ወደ ህብረተሰቡ በመቅረብ ስራ እየሰራ ከመገኘቱም በላይ የተቋቋመዉ በአካባቢዉ እና በህብረሰቡ ላይ ትርጉም ያለዉ ለዉጥ ማምታት ስለሆነ ይህም የሚረጋገጠዉ ትምህርት ላይ ላይ አተኩሮ በመሰረት እንደሆነ ያምናል፡፡በዚህ መሰረት በዚሁ ዐመት የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎችን በአራት ወረዳዎች ማለትም በደብረሲና፣ በሸዋሮቢት፣በኢሶንና በመኮይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ምርጥ ተማሪዎችን እና መምራንን በመለየት እና በበጎ አድራጂነት በማሰማራት የአካባቢዉን ትምህረትን የማገዝና የፕሮግራሙን መሰረት መጣል ይገባል፡፡በዚህ መሰረት ይህ እቅድ ተዘጋጅቷል፡፡
II. ዓላማ፡
1. በይፋት የይልማ ትምህርት ፕሮግራሙን መጀመር መቻልና ለአካባቢዉ ተስፋ ያለዉ ማህበርነቱን ማረጋገጥ፤
2. በየከተማዉ 200 ተማሪዎችን በድምሩ 800 የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን በማጠናከሪያ ትምህርት የአካዳሚክ ትምህርት ብቃታቸዉንና ተነሳሽነታቸዉን ማሳደግ፤
III. ስልት ፡
1. አስቀድሞ ስራዉን የሚያስኩትን ምርጥ ተማሪዎችን እና መምህራንን መለየትና ስለ በጎ ፍቃዱ ከእነሱ ጋር መግባባት መፍጠር፣
2. የስራዉን መነሻና መድረሻ በትክክል መረዳት መቻል እና ሳይንሳዊና ዉጤታማ የማጠናከሪያ ትምህርት ስርዓት መተግበር መቻል፣
IV. ተግባራት
1. አስፋላጊ በጀትን ማረጋገጥ፣
2. ምርጥ ተማሪዎችን እና መምህራንን ከትምህርት ቤቱ ጋር በመተባበር በዝርዝር መለየት ፣
3. የመግቢያ ፈተና ማዘጋጀትና መስጠት፣
4. የማጠናከሪያ ትምህርት ይዘትና አሰጣጥ ጋይድ ላይን ማዘጋጀት፣
5. የፕሮግራም ይዘት ላይ ለአስተባባሪ ተማሪዎችና መምህራን ኦሬንቴሽን መስጠት፣
የማየናከሪያ ፕሮግራም ማዘጋጀትና ለሁሉም መስጠት፣
6. ስራዉነወ በተመሳሳይ ጊዜ ማስጀመር፣
7. መሃል ላይ ስራዉን በጋራ መገምገም
8. ማጠቃላያ ፈተና ለተማሪዎች መስጠት
9. ጰማጠቃለያና የሰርተፊኬት ፕሪግራም ማካሄድ፣
V. የፕሮግራሙ ዋና ዋና አካላት
1. 7ቱም አስተዳደሮች፣
2. 4 ትምህርት ቤቶች፣
3. ከ9-12 ኛ ክፍል ኬወረዳዉ 200 በድምሩ 800 ተማሪዎች፣
4. ከየትምህርት ቤቱ 10 ምርጥ ተማሮዎች በድምሩ 40 ተማሪዎች፣
5. ከየትምህርት ቤቱ 2 ምርጥ መምህራን በድምሩ 8 አስተባባሪ ምርጥ መምህርን ፣
6. የ4 ትምህርት ቤት 4 ርዕሳነ መምህራን ፣
VI. በጀት
ተ.ቁ የበጀት ርዕስ የበጀት ስሌት በጀት /ብር ፈፃሚ
ተ.ቁ | የበጀት ርዕስ | የበጀት ስሌት | በጀት /ብር | ፈፃሚ |
1 | አስጠኚ ተማሪዎችን ማበረታታት | 40*2000 ብር | 80 000 | ስፖንሰር |
2 | መምህራንና ርዕሳነ መምህራንን ማበረታታት | 12*1000 ብር | 12 000 | ስፖንሰር |
3 | ኦሬንቴሽን መስጠት | 34 ሰዉ*300 ብር | 10 200 | ይልማና ዞን |
4 | የጋራ ግምገማ ማካሄድ | 34 ሰዉ*300 ብር | 10 200 | ይልማ |
5 | ለጋይድ ላን ዝግጅት | 6 ሞጁዉል*3000 | 18000 | ምርጥ መምህራን |
7 | ለክትትል ማካሄድ | 2 ሰዉ*10 ቀን* 860 | 17200 | ይልማ |
8 | ለፅ/መሳሪያና ሰርተፊኬት | 5500 | ስፖንሰር | |
ለማጠቃለያ ስነ ስርዓት ማካሄድ | 90 ሰዉ*500 ብር | 45 000 | ይልማ | |
ድምር | 198100 | |||
መጠባበቂያ | 1900 |
VII. ክትትልና ግምገማ
1. በየትምህረት ቤቱ የአቴንዳንስ ክትትል ይደረጋል፣
2. የሳምንት አጭር እና በየወሩ እንደሁም የማጠቃለያ ሪፖረት በርዕሳነ መምህራን ለይልማ በቴሌግራም ይደረጋል፣
3. ወርሃዊ ፊድ ባክ ለት/ቤቱ ይሰጣል፣
4. የሚመለከታቸዉን አካላት ሁሉ ያሳተፈ መሃል ላይ እና የማጠቃሌ ግምገማ ይካሄዳል፣