ኮንስትራሽን
በአጣዬ/ኤፌሶን እና አካባቢው በይፋት ቀጠና በደረሰው ጥቃት የተቃጠሉብንን ቤቶች መልሶ ለመገንባት መንግስት በእንቅስቃሴ ላይ ቢሆንም እጅግ በመዘግየቱ ምክንያት ተፈናቃይ ቤተሰቦቻችን አሁንም ተበትነው በስቃይ ላይ ናቸው:: ይልማ ከያዛቸው የ100 ሚሊዮን የ100ቤት ግንባታ እቅድ ውስጥ 10 የብሎኬት ቤቶችን በመንግስት በተጠናው ስታንዳርድ መሰረት ኤፌሶን ላይ ለማስጀመር እንቅስቃሴ ጀምሯል:: በቀጣይም በሁሉም አካባቢዎች በመልሶ ግንባታ አሻራውን እንዲያሳርፍ ሁሉም ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ እናስተላልፋለን::
የይልማ ስራ አስፈፃሚ ኮምቴ